Quantcast
Channel: Ethiopia Observer
Viewing all articles
Browse latest Browse all 1286

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አረፉ

$
0
0

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ቫቲካን አስታውቋል። ከደቡብ አሜሪካ የተሾሙ የመጀመርያው ሊቀ ጳጰስ የሆኑት ፖፕ ፍራንሲስ ከመተንፈሻ አካላት ህመም ጋር በተያያዘ የሕክምና ክትትል ሲደረግላቸው ነበር።

“ዛሬ ጠዋት 1:35 ላይ የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ወደ አባታቸው ቤት ተመልሰዎል።መላ ህይወታቸውን ለጌታ እና ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሰዉ ነበሩ።” በማለት ካርዲናል ኬቨን ፌሬል፣ የቫቲካን ካሜርንጎ ተናግረዋል።

“የወንጌልን እሴት በታማኝነት፣ በጀግንነት፣ እና በዓለም አቀፋዊ ፍቅር እንድንኖር አስተምረውናል፤ በተለይ ለተቸገሩና ለተገፉ እንድንቆም።” ሲሉም አክለዋል።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ህይወት ያለፈው፤ ትላንትና እሁድ ዕለት በተከበረው የትንሳዔ በዓል በቅዱስ ጴጥሮስ ለተሰበሰበው ምዕመን በአካል ተገኝተው የትንሳዔ በዓል መልዕክት ባስተላለፉ ማግስት ነው።

The post የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ አረፉ appeared first on Ethiopia Observer.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 1286

Trending Articles